ዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮችዋን ከጀርመን እያወጣች ነው

ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሜሪካ በመላው ዓለም ያላትን የሠራዊት ቁጥር ለመቀነስ መወሰናቸውን ተከትሎ ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ወደ 12ሺ የሚጠጉ ወታደሮቿን ከጀመርን እያወጣች ነው፡፡ ከዋሽንግተን የቪኦኤ ዘጋቢ ሲንዲ ሴን ያጠናቀረቸው ዘገባ እነሆ፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሜሪካ በመላው ዓለም ያላትን የሠራዊት ቁጥር ለመቀነስ መወሰናቸውን ተከትሎ ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ወደ 12ሺ የሚጠጉ ወታደሮቿን ከጀመርን እያወጣች ነው፡፡ የአሜሪካ መከላከያ ምኒስቴር ባለሥልጣናት እምርጃው የአገሪቱን ደህንነት ይበልጥ ያጠናክራል ቢሉም፣ የአሜሪካ የደህንነት ባለሙያዎች ግን፣ እርምጃው ፕሬዚዳንት ትራምፕ የመከላከያ ወጪ ድርሻቸውን ለማዋጣት ግድ የለሾች ናቸው የሚሏቸውን የኔቶ አባል አገሮች መቅጫ ነው ሲሉ ይተቹታል፡፡

በርካታ ኤክስፐርቶች ዩናይትድ ስቴት ስ ወደ 12 ሺ የሚጠጋ ወታደሮችዋን ከጀርመን ለማውጣት መወሰኗን ተዋጊ ጀቶችን ከስፔንድ ሃለም የአየር ኃይል አንስቶ ወደ ጣልያን ማንቀሳቀሷንና፣ የአውሮፓን ቀዳሚ ወታደራዊ መምሪያ ከስቱትጋርት በማንሳት ወደ ቤልጅየም ማዛወሯን ሲስሙ ባለሙያዎቹ ማመን እንዳቃታቸው ተናግረዋል፡፡
አሜሪካ በአውሮፓ ካላት ወታደራዊ የጦር ይዞታ ይህ ዓይነቱ ስርነቀል ውሳኔ ሲወስን ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡

በርካታ ኤክስፐርቶች ዩናይትድ ስቴት ስ ወደ 12 ሺ የሚጠጋ ወታደሮችዋን ከ ጀርመን ለማውጣት መወሰኗን ተዋጊ ጀቶችን ከስፔንድ ሃለም የአየር ኃይል አንስቶ ወደ ጣልያን ማንቀሳቀሷንና፣ የአውሮፓን ቀዳሚ ወታደራዊ መምሪያ ከስቱትጋርት በማንሳት ወደ ቤልጅየም ማዛወሯን
ሲስሙ ባለሙያዎቹ ማመን እንዳቃታቸው ተናግረዋል፡፡

አሜሪካ በአውሮፓ ካላት ወታደራዊ የጦር ይዞታ ይህ ዓይነቱ ስርነቀል ውሳኔ ሲወስን ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡
የአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስትር ማርክ ኤስፐር በፔንተጋን የሚከተለውን ተናግረዋል
"እነዚህ ለውጦች ዩናይትድ ስቴትስ እና የኔቶ አባል አገሮች ከሩስያ የሚገጥማቸውን ጥቃትየሚከላከሉበትን መንገድ ያጠናክራል፣ አሜሪካም የተለያዩ ስትራቴጂዎችን እንድትጠቀም እድል በመስጠት ኔቶንም እንዲጠናከር ያደርገዋል፡፡" ለአጋር አገሮችም ዋስትና ይሰጣል፡፡ የአሜሪካና የአውሮፓ ወታደራዊ ማዕከላትም የጋራ ልምምዶቻቸውን በተለያየ ስልት እንዲያደርጉ ይረዳቸዋል፡፡
ይሁን እንጂፕሬዚዳንት ትራምፕ ከዋይት ሃውስ በሰጡት መግለጫ ግን ለስር ነቀል ለውጡ፣ ሌሎች ምክንያቶች ያሏቸው መሆኑን፣ እንዲህ በማለት በግልጽ ተናግረዋል

"ጀርመን ለኔቶ መክፈል የነበረባት በቢሊዮን የሚቆጠር እዳ አለባት፡፡ እና ታዲያ እነዚያን ሁሉ ወታደሮች እዚያ ማኖር ያለብን ለምንድነው? ይኸው አሁን ጀመርኖች ይሄ እምርጃ ለኢኮኖሚያቸው ጥሩ አለመሆኑን እየተናገሩ ነው፡፡ ለኛ ኢኮኖሚ ግን ጥሩ ነው፡፡ ጀርመን ግድየለሽ ናት፡፡"

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ጀመርንን እንደ ኢኮኖሚ አጋር አገር ከመመልከት ይልቅ እንደ ስጋት እየተመለከቱለረጅም ጊዜ ጀምሮ የሰላ ትችት ሲሰነዝሩ መቆየታቸውን ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ከጀመርንዋ መሪ ቻንሰለር አንጀላ ማርኬልም ጋር የቀዘቀዘ ግንኙነት እንደንበራቸው ያነሳሉ፡፡

ከአትላንቲክ ባሻገርጉዳዮች ላይ ባለሙያ የሆኑ አንዳንድ ኤክስፐርቶች ይህ ውሳኔ በአሜሪካና በጀርመን ግ ንኙነት ላይ ከፍተኛ አደጋ የሚያመጣ የኔቶ አባል አገሮችን እሚያዳክም ና የሩሲያውን ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሚያስደስት ነው ይላሉ፡፡ የአትላንቲክ ካውንስ ኤክስፐር የሆኑት ማርክ ስማኮቭስኪ እንዲህ ብለዋል

በጀርመን በዩናይትድ ስቴትስና በአውሮፓ ብቻ ሳይሆን እንዲሁም ከጀመርና ጋር ጭምር ለአስርት ዓመታት የግንኙነታችን ዋና መሠረትና ሆነው የኖሩትን የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳሚ መምሪያዎችን መዝጋት ማለት የአሜሪካንን ደህንነትና ፍላጎት አደጋ ላይ መጣል ነው፡፡ በዚህ ረገድ ይህ አስተዳደር እየሄደበት ያለበትን ፍጥነት እየተመለከቱ የሚገረሙ ወገኖችም ያሉ ይመስለኛል፡፡
ሌሎች ኤክስፐርቶች ደግሞ እርምጃው ከጀርመን ወይም ከአውሮፓ ይልቅ በአብዛኛው የራሷን የአሜሪካንስትራቴጅክ ጥቅም የሚጎዳ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ ለምሳሌ ከጀርመን ማርሻል ፈንድ ብሩኖ ለቴ እንዲህ ይላሉ

"ጀመርን ለረጀም ጊዜ የቆየና አሁንም ድረስ አሜሪካ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ለምታደርጋቸው ተልእኮዎችና እንቅስቃሴዎች በሙሉወሳኝና ቁልፍ ማዕከል ነች፡፡ እዚያ እጅግ አስፈላጊ የሆኑ የማደራጃ ወይም የሎጀስቲክስ ማዕከሎች እና የማዘዣ ጣቢያዎች አሉ፡፡ ከዚህ ማዕከል ሠራተኞችን እምትቀንስ ከሆነ ፈጥኖ ደራሽነትህ ቀርቶ በምትሰጠው ምላሽ ሁሉ እጅግ አዝጋሚ ትሆናለህ፡፡"

የደህንነት ባለሙያዎች እንደሚሉት እንዲህ ያለው መጠነ ሰፊ የወታደራዊ ተቋማት ዝውውር ብዙ ቢሊዮን ዶላሮችን እሚያስወጣና የዴሞክራቲክ ፓርቲ ፕሬዚዳንት እጩ የሆኑ ጆ ባይደን የጥቅምቱን ምርጫ ቢያሸነፉና ወደነበረበት እንኳ ለመመለስቢያስፈልግ በርካታ ዓመታትን ሊወስድ የሚችል ነገር ነው፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮችዋን ከጀርመን እያወጣች ነው