ዲፕሎማቶችና የተለያዩ አገር ዜጎች ከሱዳን መውጣት ቀጥለዋል

Your browser doesn’t support HTML5

በሱዳን በሁለቱ ተቀናቃኝ ወገኖች መካከል ያለው ጦርነት መቀጠሉን ተከትሎ የተለያዩ ሀገራት ዜጎቻቸውን እና ዲፕሎማቶቻቸውን ከሱዳን ዋና ከተማ፣ ካርቱም ማስወጣታቸውን ቀጥለዋል። መብራት፣ ውሃ እና የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠባቸው በካርቱም እና አካባቢዋ የሚኖሩ ሱዳናውያን ደግሞ

ከውጊያው ለማምለጥ አደገኛ በሆኑ ጎዳናዎች፣ በመኪና እና በእግር ለመውጣት ጥረት እያደረጉ ናቸው። የሱዳን ጦር ኃይሎች እና አር ኤስ ኤፍ በመባል የሚጠራው ፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ልዩ ኃይል መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት፣ 264 ሲቪሎችን ጨምሮ እስካሁን ከ420 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ከ3ሺህ 700 በላይ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ተገልጿል።

/ዘገባው በአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ፣ ሮይተርስ እና አሶሽየትድ ፕሬስ የተጠናቀረ ነው። ስመኝሽ የቆየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች/