የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዘመቻዎችና የገንዘብ ሚና

2012 Election banner en 308

ስድስት ቢሊዮን ዶላር የፈሰሰባቸው የ2 ሺህ አሥራ ሁለቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዛንታዊ ምርጫ ዘመቻዎች፥ የከሰቷቸው አዳዲስና ነባር ፈተናዎች ይመረመራሉ።

Your browser doesn’t support HTML5

ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዘመቻዎችና ገንዘብ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተገባዶ፥ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በሁለተኛ ዙር የአስተዳደር ዘመናቸው ሊያሳኳቸው የሚያስቧቸው ክንውኖች ውጥኖች ዳር ለማድረስ ከተፎካካሪው የሪፐብሊካን ፓርቲ የምክር አባላት ጋር በትብብር በሚያስችሉ መንገዶች ላይ መነጋገር ይዘዋል።

በአንጻሩ፥ እጅግ ከፍተኛ ፉክክር የታየበትና ታሪካዊ የተባለው ምርጫ፥ የሁለት ወገን ዘመቻዎች አካሄድ በውጤቱ ላይ የነበራቸው ሚና፤ የተደረጉና ያልተደረጉ፤ ሊሆኑ የሚገቡትን ጨምሮ መጪውን ከወዲሁ ለመቃኘት የሚረዱ ፍተሻዎች በሁሉም ጎራ እየተሞከሩ ይመስላል።

በተቀናቃኝ ጎራ የተሰለፉት ቡድኖች በየበኩላቸው የምረጡኝ ዘመቻዎቻቸውን ለማቀላጠፍ፥ ለቴሌቭዥን ማስታወቂዎች ያፈሰሱት እጅግ የተጋነነ መጠን ያለው ገንዘብ በማነጋገር ላይ ነው።

ሁለት የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን፥ ዶ/ር ጌታቸው መታፈሪያ ዋሽንግተን አቅራቢያ ከሚገኘው የሞርጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ፤ እንዲሁም ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማሪያም፥ ከካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ለሞያዊ ትንታኔ ተጋብዘዋል።