ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንትነት የሚወዳደሩት እጩዎች ዛሬ ለመጀመርያ ጊዜ ክርክር ያካሂዳሉ

ሬፓብሊካኑ እጩ ዶናልድ ትራምፕ(ግራ) ና ዴሞክራቷ ሂለሪ ክሊንተን (ቀኝ)

ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንትነት የሚወዳደሩት ሬፓብሊካኑ እጩ ዶናልድ ትራምፕና ዴሞክራቷ ሂለሪ ክሊንተን ከሦስቱ አንዱና የመጀመያው የሆነውን የቴሌቪዥን ክርክር ዛሬ ማታ ሄምስትድ ኒውዮርክ ውስጥ ያካሂዳሉ።

የሁለቱ የዛሬ ማታው ክርክር፣ በዚህ የተቀራረበ ውጤት እንዳለው በሚነገርለት ውድድር ውስጥ፤ ማንኛቸው ለቤተ-መንግሥቱ እንደሚቀርቡ ወሳኝ የሆነ አንደምታ እንደሚኖረው ተገምቷል።

የዛሬው የመጀመሪያው ክርክር፣ ከሂለሪ ክሊንተን ጋር የነበራቸውን ሰፊ ልዩነት ላጠበቡት ለዶናልድ ትራምፕ ትልቅ ትርጉም ይኖረዋል ተብሏል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንትነት የሚወዳደሩት እጩዎች ዛሬ ለመጀመርያ ጊዜ ክርክር ያካሂዳሉ