ባራክ ኦባማ "የፅናት ተምሳሌት" ሽልማት ተቀበሉ

Your browser doesn’t support HTML5

የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ትላንት ዕሁድ ባደረጉት ንግግር የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባለት ከፓርቲያቸው አቋም ጋር ቢጣረስም ዕውነቱን መርምረው ሃቅ እንደሚናገሩ ጥልቅ ምኜቴ ነው ብለዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዚዳንት ትላንት ይህን አስተያየት የሰጡት ቦስተን ከተማ ውስጥ የጆን ኤፍ ኬኔዲን ፕሮፋይል ከሬጅ በቁም ትርጉሙ የፅናት ተምሳሌት የተባለ ሽልማት በተቀበሉበት ወቅት ነው፡፡