አሜሪካ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የሚውል ተጨማሪ የ35 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገች

  • እስክንድር ፍሬው

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (United States Agency for International Development/USAID)

ዩናይትድ ስቴትስ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያዊያን የሚሆን የ35 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ድጋፍ ዛሬ ይፋ አድርጋለች።

ዩናይትስ ስቴትስ ዛሬ ይፋ ያደረገቸው ተጨማሪ ድጋፍ የበልጉን ግምገማ ተከትሎ የተከለሰው የሰብዓዊ እርዳታ ሰነድ ይፋ ከተደረገ በኃላ የመጀመርያው ነው።

ይህንኑ ሰነድ ባለፈው ሳምንት ይፋ ያደረጉት መንግሥትና አጋሮቹ 10.2 ሚሊዮን የነበሩት የተረጂዎች ቁጥር ወደ 9.7 ሚሊዮን ዝቅ ማለቱን ጠቁመዋል።የነዚህን ተረጂዎች ፍላጎት እስከ መጪው ታህሳስ ወር ለሟሟላት የ600 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።

ዛሬ ይፋ የተደረገው የዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ ይሄንኑ የሚያግዝ ነው።ድጋፉን ይፋ ያደረጉት በኢትዮጵያ የዩስኤድኣይዲ ዳይሬክተር ለስሊ ሪድ ናቸው።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

አሜሪካ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የሚውል ተጨማሪ የ35 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገች