”ከፍታ” የተሰኘ አዲስ የወጣቶች ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

Your browser doesn’t support HTML5

ከአሜሪካ መንግሥት በተገኘ የ3.1 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ29 ዓመት በታችና ከ15 ዓመት በላይ የሆኑ 2ሚሊዮን ወጣቶችን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ፡፡ አምሬፍ ሄልዝ አፍሪካ በተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት አስተባባሪነት የሚፈጸመው ፕሮጀክት የወጣቶችን የሥራ ፈጠራና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፣ የሲቪልና ማኅበራዊ ተሳታፊነት፣ የሥነ ተዋልዶና ጤና አገልግሎት ተደራሽነት ያረጋግጣል ተብሏል፡፡

ሰሞኑን ይፋ የተደረገውና ከፍታ የሚል ስያሜ የተሰጠው ፕሮጀክት በኢትዮጵያ 18 ከተሞች ላይ ተግባራዊ እንደሚሆን የአምሬስ አፍሪካ አስተባባሪ ቻላቸው ጥሩነህ ለአሜረካ ድምጽ አስታውቀዋል፡፡