'አዎ፤ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ በመምጣቴ ተፀፅቻለሁ'- ቬንዝዌላዊት ስደተኛ

Your browser doesn’t support HTML5

ነፍሰ ጡሯ ቬንዝዌላዊት ሮዛ ከሃገሯ ተነስታ ዩናይትድ ስቴትስ ድንበር የደረሰችው አራት ወር ሙሉ በእግሯ ተጉዛ ነው።

በብዙ የደቡብ አሜሪካ ሀገሮች እያቆራረጠች የደረሰችው ሮዛ አሁን ግን "ለምን መጣሁ!?!" እያለች ትፀፀታለች።

የቴክሳስ ግዛት ሪፐብሊካን አገረ ገዢ ወደ ዋሺንግተን ዲሲ በአውቶቡስ አሳፍረው ከላኳቸው ፍልሰተኞች አንዷ ስትሆን አሁን ያለችው ዴላዌር ግዛት ውስጥ ነው።

የቬንዝዊላዊቱንና የኑሮ ጓደኛዋን ታሪክ የያዘውን ሪፖርተራችን አላይን ባሮው ያጠናቀረውን ዘገባ ቆንጅት ታየ ለዛሬ አሜሪካና ህዝቧ ፕሮግራም አሰናድታዋለች።