“በኢትዮጵያና ኤርትራ የሰብአዊ መብት አያያዙ እንደከፋ ነው” - ዩኤስ

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናዩትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሀገራትን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በተመለከተ የሚያወጣውን ዓመታዊ ሪፖርት በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትላንት ሚያዚያ 14/ 2016 ዓ.ም ባወጣው የሀገራትን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በሚተነትነው ሰፊ የአውሮፓያኑ የ2023 ዓመታዊ ሪፖርቱ፤ ፣የኢትዮጵያ መንግሥት ወይም የመንግሥት ወኪሎች፣ ከሕግ ውጪ የዘፈቀደ ግድያ መፈፀማቸውን ፣ በርካታ የሃገር ውስጥና የውጪ ሃገራት የሰብአዊ መብት ቡድኖች ሪፖርት ጠቅሶ ይፋ አድርጓል።

ግድያዎችቹ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል እየተካሄዱ ባሉ ግጭቶች እንዲሁም ትግራይን ጨምሮ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የተፈጸሙ እንደሆነ አስታውቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ፡፡