"ኦባማ ኬር" እና መለወጫው

Your browser doesn’t support HTML5

በዩናይትድ ስቴትስ ኮንግሬስ ያሉ ሪፖብሊካውያን ባለፉት ሰባት ዓመታት ቃል በገቡት መሠረት ኦባማ ኬር እየተባለ የሚጠራውን የጤና ጥበቃ ሕግ ሠርዘው በሌላ እንዲተኩ ውጥረት ውስጥ ገብተዋል። ባለፈው አስተዳደር የወጣው ሕግ ቀድሞ የጤና መድኅን ያልነበራቸው ብዙ አሜሪካውያን በተመጣጣኝ ዋጋ የጤና ጥበቃ አገልግሎት ማግኘት ያስችላቸዋል።