አምስት አባላት ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ቡድን ወደ አዲስ አበባ ያመራል

Your browser doesn’t support HTML5

አምስት አባላት ያሉት አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ቡድን የወቅቱን የፖለቲካ ሁኔታ ለመከታተልና በሃገሪቱ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝና እና በዴሞክራሲ ላይ ያተኮረ ጉብኝት ለማድረግ ነገ ወደ ኢትዮጵያ ያመራል። በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ የሚጠይቀውን /ኤችአር 128/ የተባለውን የዩናይትድ ስቴትስ ረቂቅ ሕግ ያቀረቡት ኮንግሬስማን ክሪስ ስሚዝ አንደኛው የልዑካኑ ቡድን አባል ናቸው።