“አሜሪካ ቀድሞውንም ታላቅና ጠንካራ ናት” .. የዲሞክራቲክ ፓርቲ ጉባኤ ሦሥተኛ ቀን

በዩናይትድ ስቴስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ጉባኤ የትላንቱ ሦሥተኛ ቀን ምሽት ዋናው ተናጋሪ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ናቸው።

ፕሬዝደንቱ በትላንቱ ንግግራቸው በተደጋጋሚ የሬፖብሊካኑን እጩ ተወዳዳሪ ዶናልድ ትራምፕን ክፉኛ ነቅፈዋል።

ሚስተር ትራምፕ “ሰዎችን በዘር የመከፋፈል ሃሳብ አራማጅ፤ ፍርሃትና ሃሳብ መንዛትን ዋና መለያቸው ያደረጉ .. መሪ ለመሆን ፈጽሞ ብቃት የሌላቸው ሰው ናቸው” ሲሉ ገልጸዋቸዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህን በተናገሩበት ወቅት የጉባዔው ተሳታፊዎች ሂላሪ ክሊንተን ኦባማን የምትተካ ብቸኛዋ ሰው ናት ሲሉም በሆታ ገልጠዋል።

ፕሬዝዳንት ኦባማና ሌሎች “ባለ ከባድ ሚዛን” የፓርቲው አባላት “ተፎካካሪ የላቸውም” ያሏቸውን ዕጩዋቸውን የሴናተር ሂላሪ ክሊንተንን ብቃት በማጉላትና የተቀናቃኛቸውን “ደካማ” ያሉትን ማንነት በመንቀፍ የተናገሩበት ሦሥተኛ ቀን በወፍ በረር ሲቃኝ።

ዝርዝር ዘገባውን ከዚህ ያዳምጡ፤

Your browser doesn’t support HTML5

“አሜሪካ ቀድሞውንም ታላቅና ጠንካራ ናት” .. የዲሞክራቲክ ፓርቲ ጉባኤ ሦሥተኛ ቀን