አሜሪካ በኤርትራ ባለሥልጣን ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ ክልል ውስጥ በተካሄደው ሺዎች የሚቆጠሩ ተገድለውበታል ከ 2 ሚሊዮን በላይ ተፈናቅለውበታል በሚባለው ግጭት ተፈፅሟል በተባለው ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ውስጥ “ተሳትፈዋል” በሚል በወነጀለቻቸው የኤርትራ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሃንስ ላይ ማዕቀብ መጣሏን ዩናይትድ ስቴትስ ዛሬ አስታውቃለች። ይህንን የዩናይትድ ስቴትስን እርምጃ “ተቀባይነት የሌለው ነው” ሲል የኤርትራ መንግሥት ኮንኗል።