የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግሬስ የተጎጂዎች ቤተሰቦች በሳዑዲ አረቢያ ላይ ክስ መመሥረት የሚያስችል ሕግ አጸደቀ

  • ሰሎሞን ክፍሌ
የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግሬስ እአአ መስከረም 11, 2001 ዓ.ም. ለተፈጸመው የሽብር ጥቃት፥ የተጎጂዎች ቤተሰቦች በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ላይ ክስ መመሥረት እንዲችሉ የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አጸደቀ።

ሕጉን በሥልጣናቸው ውድቅ እንደሚያደርጉት ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ዝተው የነበረ ቢሆንም፥ ምክር ቤቱ ሕጉን ያሳለፈበት የድምፅ ብዛት ያንን የፕሬዘዳንቱን ሥልጣን ማቆም የሚችል ሆኗል።

ባራክ ኦባማ በፕሬዘዳንታዊ ሥልጣናቸው ያሳለፉት ሕግ በኮንግሬሱ ውድቅ ሲደረግ የትላንቱ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግሬስ የተጎጂዎች ቤተሰቦች በሳዑዲ አረቢያ ላይ ክስ መመሥረት የሚያስችል ሕግ አጸደቀ