ትናንት የተጀመረው የጃንዋሪ 6 አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርት

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች ምክር ቤት የጃንዋሪ 6 አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርቱን ለሕዝብ ማቅረብ ጀመረ።

ኮሚቴው ይህንን ሪፖርቱን ማቅረብ የጀመረው ወደ ማጣራት ሥራው ከገባ ወደ አንድ ዓመት ከሚጠጋ ጊዜ በኋላ ነው።

ኮሚቴው ግኝቶቹን፣ ማስረጃዎችንና እማኞችን የሚያሰማው በመጭዎቹ ወራት መደዳውን እንደሚሆን ተነግሯል። የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሥልጣን እንደያዙ ለመቆየት ደጋፊዎቻቸው ምክር ቤቱን በኃይል እንዲወርሩ እንዳደረጉ ለአሜሪካ ሕዝብ ያስረዳበትን የምርመራውን ውጤት በተመለከተ የቪኦኤዋ የምክር ቤታዊ ጉዳዮች ዘጋቢ ካትሪን ጂፕሰን ያጠናቀረችውን ዘገባ ቆንጅት ታየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች።