የዩናይትድ ስቴትስ እና የቻይና የንግድ ግንኙነት ሥምምነት

  • ቪኦኤ ዜና

የዩናይትድ ስቴትስይ የንግድ ተወካይ ሮበርት ላይትዘር

የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛው የንግድ ባለሥልጣን ዛሬ ረቡዕ በሰጡት ቃል፣ ከቻይና ጋር ያለው የንግድ ግንኙነት ሥምምነት ገና ዳር አልደረሰም አሉ።

ዋሺንግተን ውስጥ በተካሄደ ምክር ቤታዊ ውይይት፣ ሥምምነት ላይ ለመድረስ፣ ብዙ መሠራት ያለባቸው ነገሮች አሉ ያሉት የዩናይትድ ስቴትስይ የንግድ ተወካይ ሮበርት ላይትዘር ጅምራችንን ዳር ለማድረስ ከተፈለገ፣ ወዳጅነታችንን ሊያሻሽሉ የሚችሉ ጉዳዮችን መስመር ማዝያዝ ያስፈልጋል ብለዋል።

ዓለማችን ትልቆቹ የኢኮኖሚ ባለቤቶች ዩናይትድ ስቴትስ እና ቻይና፣ አዲስ ሥምምነት ላይ ለመድረስ ለወራት የዘለቀ ድርድር ማካሄዳቸው ይታወቃል። የሁለቱም ወገን ተደራዳሪዎች፣ ጥሩ ጅምር ላይ እንዳሉ ግን የአሜሪካው ተወካይ ላይትዘር አመልክተዋል።