የታይዋን ጉዳይ በባይደን እና ሺ ፒንግ ውይይት ዋና አጀንዳ ነበር

Your browser doesn’t support HTML5

የአሜሪካው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በታይዋን ጉብኝት ሊያደርጉ ይችላሉ የሚለው ዜና መሰማት ከጀመረ ጀምሮ በአሜሪካና ቻይና መሃል ውጥረት አይሎ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ፕሬዝደንት ጆ ባይደንና የቻይናው አቻቸው ሺ ጂንፒንግ ትናንት ሃሙስ ረዘም ያለ የስልክ ውይይት አድርገዋል።

ናንሲ ፔሎሲ በታይዋን ጉብኝት የሚያደርጉ ከሆነ አሜሪካ “ጠንከር ያለና የማይቀር የአጸፋ እርምጃ ይጠብቃታል” ስትል ቤጂንግ አስጠንቅቃለች።