ከህንድ ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነት እንደሚፈጠር የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ፣ ሁለቱ ሀገሮች፣ በወዳጅነት መንፈስ፣ ልዩነቶቻቸውን በንግድና በሌሎች ጉዳዮች እንደሚፈቱ ተስፋችውን ገልፀዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የአሜሪካው ከፍተኛ ዲፕሎማት፣ ከህንዱ አቻቸው ኤስ ጃይ ሻን ካር እና ከህንዱ ጠ/ር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ዛሬ ረቡዕ በተገናኙበት ወቅት ነው ይህን ያስታወቁት።
ጠ/ሚኒስትር ሞዲ ድጋሜ ከተመረጡ ወዲህ፣ የሁለቱ ሀገሮች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሲገናኙ ይሄ የመጀመሪያ መሆኑ ነው።