ፓትሪሺያ ሃስላክ የአምባሳደርነት ጊዚያቸውን አጠናቀቁ

  • ቆንጂት ታየ

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደርነት ጊዚያቸውን ያጠናቅቁት ፓትሪሺያ ሃስላክ

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደርነት ጊዚያቸውን የሚያጠናቅቁት ፓትሪሺያ ሃስላክ ትናንት በኤምባሲው የስንብት ንግግር አድርገዋል።

አምባሳደርዋ በኢትዮጵያ ባሳለፉት የሦሥት ዓመታት የሥራ ዘመን በኢትዮጵያ በሃምሳ ዓመታት ውስጥ ባልታየ መልኩ የተከሰተው ድርቅ የከበደ ረሃብ እንዳያስከትል የተደረገው ጥረት ከተከናወኑት አኩሪ ተግባራት አንዱ መሆኑን ማስተዋላቸውን ገልጸዋል።

በቅርብ ጊዚያት በኢትዮጵያ የተከሰቱት ሁኔታዎች እንደሚያሳስቡዋቸው የገለጹት አምባሳደርዋ በጉዳዩ ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግስሥት ጋር መነጋገራቸውን እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።

ተሰናባችዋ የዩናይትድ ስቴትስ አማባሳደር በንግግራቸው በሀገሮቻችን ግንኙነት ዋና ዋና ምሰሶዎች በሆኑት በልማትና የምጣኔ ሃብት ዕድገት፡ በሰብዓዊ መብት እና መልካም አስተዳደር እንዲሁም በሰላምና ፀጥታ “ጉዳዮች አትኩረን ባከናወንናቸው ሥራዎች እጅጉን እኮራለሁ ፡ ገና ብዙ ስራ እንደሚጠብቀንም በሚገባ አውቃለሁ” ብለዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ፓትሪሺያ ሃስላክ የአምባሳደርነት ጊዚያቸውን አጠናቀቁ