ዩናይትድ ስቴትስ ትልቅ የተባለውን ፈንጂ በአፍጋኒስታን ጥላለች

Your browser doesn’t support HTML5

በትናንትናው ዕለት ዩናይትድ ስቴትስ በጦር መሣሪያ ካዝናዋ ከኑክሌር ቦምብ ውጭ ትልቁ የተባለውን ፈንጂ በአፍጋኒስታን ጥላለች። ጥቃቱ በምሥራቃዊ አፍጋኒስታን ናንገሃር ግዛት እራሱን እስላማዊ መንግሥት ነኝ ብሎ የሚጠራው አይሲስ ይጠቀምባቸው በሚል መረጃ የተገኝባቸው ዋሻዎች ላይ ያነጣጠረ ነው። የዩናይትድ ስቴይስ ወታደራዊ ባለሥልጣናት በጥቃቱ ምን ያህል የአይሲስ ተዋጊዎችና ሠላማዊ ሰዎች እንደተገደሉ መረጃ የለንም ብለዋል።