የስልጣን ዘመን ማብቂያ! የስልጣን ሽግግር!

Your browser doesn’t support HTML5

ነገ በዋሽንግተን ዲሲ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣናቸውን ያስረክባሉ። ከነገ ጀምሮ የዩናይትድ ስቴትስ 45ኛ ፕሬዚዳንት የሚሆኑት የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች በስነስርዓቱ ላይ ለመገኘት ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት ቁጥራቸው የበዛ የትራምፕ ተቃዋሚዎችም የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ናቸው።