ስለ አስትራዜኔካ እና ስለ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባቶች ማወቅ ያለብዎ!

ፕሮፌሰር ብስራት ኃይለመስቀል

ላለፉት 11 ቀናት ለጊዜው ጥቅም ላይ መዋሉ እንዲቋረጥ ተድርጎ የነበረውን የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ገደቡ ተነስቶ አገልግሎት ላይ ይውል ዘንድ የዩናይትድ ስቴትሱ የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል /CDC/ የክትባት አዋቂዎች መማክርት ቡድን መከረ።

አንድ ጊዜ ብቻ የሚሰጠው ይህ ክትባት በተለምዶው አሰራር የመድሃኒቶችን ጠባይ የሚጠቁሙ የማስጠንቀቂያ መረጃዎች በሚቀርቡበት መንገድ ከሰፈረበት ወረቀት አብሮ እንዲቀርብ እና ጥቅም ላይ እንዲውል ነው ቡድኑ የመከረው።

ለመሆኑ በቅርቡ ብሪታንያ ሰራሹን አስትራዜኔካን እና አሁን መልሶ ስራ ላይ እንዲውል የተፈቀደውን የዩናይትድ ስቴትሱን የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የጸረ ኮቪድ ክትባቶች በወሰዱ ጥቂት ሰዎች ላይ የታየው የጎንዮሽ ጉዳት ጠባይ፡ ምንነት እና አንድምታ ምን ይመስላል?

የክትባቱን ጠቀሜታ እና የዚህን በአንዳንድ ሰዎች ላይ የታየ .. ብዙዎችንም ያነጋገረ የጎንዮሽ ጉዳት ጋራና ቀኝ ለማየት የታለመ ከመስኩ ባለሞያ ጋር የተካሄደ ቃለ ምልልስ ነው።

ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን ፕሮፌሰር ብስራት ኃይለመስቀል በዋሽንግተን ዲሲው የሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ የክሊኒካልና ፋርማሲ ሳይንስ መምህር እና የትምሕርት ክፍሉ ምክትል ሊቀመንበር ናቸው።

ዝርዝሩን ከተያያዙት የድምጽ ፋይሎች ይከታተሉ።

Your browser doesn’t support HTML5

ክፍል አንድ .. የድንገተኛ ህክምና ክፍል ሃኪሙ የኮቪድ 19 ማስታወሻዎች

Your browser doesn’t support HTML5

ክፍል ሁለት .. የድንገተኛ ህክምና ክፍል ሃኪሙ የኮቪድ 19 ማስታወሻዎች