የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ከዩክሬን በቅርብ ርቀት ሰፍረዋል

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች በምስራቃዊ ፖላንድ ከዩክሬን ድንበር በቅርብ ርቀት በሚገኙ ተራራማ ደኖች ውስጥ ሰፍረዋል። ያሉበት ስፍራ በቅርቡ ሩስያ የጥቃት ዒላማ ባደረገቻቸው የምዕራባዊ ዩክሬን አካባቢዎች ቀረብ ያለ ሲሆን ኔቶ ጦርነቱ ውስጥ ቢገባ የጥቃት ዒላማ ሊሆኑ እንደሚችሉ የቪኦኤው ሄንሪ ሪጅዌል ከፖላንዷ አርላሞቭ ከተማ ባጠናቀረው ሪፖርት ዘገቧል።