አፍሪካዊያን በዩክሬን ቀውስ ውስጥ የገጠሟቸው ችግሮች

Your browser doesn’t support HTML5

ዩክሬን ውስጥ የሚገኙ አፍሪካዊያን ደኅንነታቸው ሊጠበቅ ወደሚችሉ ሃገሮች እንዳያልፉ በዩክሬን ድንበር በኩል የመታገዳቸው ነገር በጥልቅ እየረበሻቸው መሆኑን የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር፣ የሴኔጎል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳልና የኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህሜት አስታወቁ። ሁለቱ ሊቃነመንበር ማምሻውን በጋራ ባወጡት መግለጫ በግጭት ጊዜ ሁሉም ሰው ዓለምአቀፍ ድንበሮችን የማቋረጥ መብት እንዳለው አስታውሰው አሁንም በዩክሬን ግጭት ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ ዜግነታቸውና ዘራቸው ግምት ውስጥ ሳይገባ የዚህ መብት ተገልጋይ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል።