በኡጋንዳ የተከሰተው ኢቦላ በቁጥጥር ስር መሆኑንና የመንቀሳቀስ ገደብ አስፈላጊ አለመሆኑንን ፕሬዝዚዳት ዩዌሪ ሙሰቪኒ ለሀገራቸው ህዝብ በድጋሚ አረጋግጠዋል። የሃገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ‘የሱዳን ኢቦላ’ ተብሎ በተሰየመው የኢቦላ በሽታ ዓይነት ከተያዙት 31 ሰዎች ውስጥ ስድስቱ መሞታቸውን አረጋግጧል።
የኡጋንዳ የጤና ማኅበር በበኩሉ አንዳንድ አባላቱ በጸና መታመማቸውን ጠቅሶ፣ በቂ ያልሆነ የጥንቃቄ መሳሪያዎች እጥረት አለ በሚል በተለማማጅ ሃኪሞች የተጠራውን አድማ ሊቀላቀል እንደሚችል አስጠንቅቋል።
ሃሊማ አቱማኒ ከካምፓላ ያደረስችንን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።