የሰሜን ኮሪያና የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንቶች ስብሰባ

  • ቪኦኤ ዜና
የፊታችን ዓርብ የሚደረገው የሰሜን ኮሪያና የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንቶች ስብሰባ የመጨረሻ ግብ ሰሜን ኮሪያ የኒኩሌር ጦር መሣሪያ መርኃ ግብሯን ሙሉ በሙሉ እንድታቆም ማድረግ መሆኑን ዋይት ሃውስ ዛሬ አስታውቋል።

የፊታችን ዓርብ የሚደረገው የሰሜን ኮሪያና የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንቶች ስብሰባ የመጨረሻ ግብ ሰሜን ኮሪያ የኒኩሌር ጦር መሣሪያ መርኃ ግብሯን ሙሉ በሙሉ እንድታቆም ማድረግ መሆኑን ዋይት ሃውስ ዛሬ አስታውቋል።

በስብሰባው ላይ ለመገኘት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕም ወደዚያው እንደሚጓዙ ይታወቃል።

ዋሺንግተን በፕዮንግያንግ ላይ ከፍተኛ ጫና የማሳደር ዘመቻዋን እንደምትገፋበትም የዋይት ሃውሷ ቃል አቀባይ ሳራ ሃከቢ ሳንደርስ ዛሬ ለጋዜጠኞች ገልፀዋል።

“የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ኒኩሌር የጦር መሣሪያና አሕጉር አቋራጭ ሚሳይሎች ሙከራዎቻቸውን ለማቆም መወሰናቸውን ማስታወቃቸው በትክክለኛ አቅጣጫ እየተደረገ ያለ ታላቅ እርምጃ ነው” ብለዋል ሚስ ሃከቢ ሳንደርስ።