ትረምፕ ሥልጣናቸውን ያለአግባብ ተጠቅመዋል ሲሉ ናንሲ ፐሎሲ ተናገሩ

  • ቪኦኤ ዜና
የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ናንሲ ፐሎሲ

የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ናንሲ ፐሎሲ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ሥልጣናቸውን ያለአግባብ ተጠቅመዋል ሲሉ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ናንሲ ፐሎሲ አስታወቁ።

በዲሞክራት አባላት የሚመራው የምክር ቤቱ የፍትህ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ፕሬዚዳንቱ ላይ ክስ እንዲመሰረት የሚያስችሉ አንቀጾችን እንዲያዘጋጁ አፈ ጉባዔዋ ጠይቀዋቸዋል።

ፐሎሲ ይህን ያደረጉት አፈ ጉባዔው ዛሬ በቴሌቭዝን በተላለፈ መግለጫ ነው። ትናንትና ሦስት የህግ መንግሥት ምሁራን የተወካዮች ምክር ቤት ፍትህ ኮሚቴ ፊት ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን ሰጠተዋል።

ሦስቱ ምሁራን ፕሬዚዳንቱ ለራሳቸው የፖለቲካ ጥቅም ሲሉ ዩክሬይን በተቀናቃኛቸው ላይ ምርመራ እንድትከፍት ግፊት በማድረጋቸው ከሥልጣን የሚያሰናብት ጥፋት ፈጽመዋል ብለዋል። አራተኛው በትረምፕ ደጋፊ ሪፖብሊካኖች የተጠሩት ምሁር በበኩላቸው ከሥልጣን ለማውረድ የሚያደርስ በቂ ማስረጃ የለም ብለዋል።