የተመድ የፀጥታው ጥበቃ ም/ቤት ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር ይገናኛሉ

  • ቪኦኤ ዜና
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ

የተመድ የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ዛሬ ሰኞ ዋሺንግተን ውስጥ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር እንደሚገናኝና ዋይት ኃውስ በሚያዘጋጀው የምሳ ፕሮግራም ላይ ስለ ኢራን የሚሳይል ጉዳይም እንደሚወያዩ ተገለፀ።

የተመድ የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ዛሬ ሰኞ ዋሺንግተን ውስጥ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር እንደሚገናኝና ዋይት ኃውስ በሚያዘጋጀው የምሳ ፕሮግራም ላይ ስለ ኢራን የሚሳይል ጉዳይም እንደሚወያዩ ተገለፀ።

በድርጅቱ የዩናይትድ ስቴትሷ አምባሳደር ኒኪ ሄሊ ባለፈው ታህሣሥ ወር ዋሲንግተን ወታደራዊ ጦር ሰፈር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠቀሱት ስለተባለው የኢራን ሚሳይል፣ ለምክር ቤቱ አባላት ያስረዳሉም ተብሎ ይጠበቃል።

አምባሳደሯ በዚያ ጋዜጣዊ መግለጫቸው፣ ኢራን፣ የመን ውስጥ የሚገኘውን የሁቲ ሽምቅ ተዋጊዎች በህገወጥ መንገድ እንደምታስታጥቅ ወታደራዊ ጦር መሣሪያዎቹ ያስረዳሉ ብለዋል።