የኦርኬስትራ ኢትዮጵያው መሪ፥ አንጋፋው የሙዚቃ ሠው ተስፋዬ ለማ አረፈ።

Tesfaye Lemma

«ከአርባ ስድስት ዓመታት በፊት የአሜሪካ የሰላም ጓድ ሆኜ ወደ ኢትዮጵያ በተጓዝኩበት ጊዜ በኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ ስማረክ የተዋወቅኩት ተሥፋዬ ለማ ለኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ ከፍተኛ አስተዋጽ ያደረገ ሰው ነው።» ቻርልስ ሳተን።

Your browser doesn’t support HTML5

ቆይታ ከተሥፋዬ ለማ የእድሜ ልክ ወዳጅ፥ Charles Sutton ጋር


Your browser doesn’t support HTML5

ቆይታ ከሁለገቧ አርቲስት ዓለም ጸሃይ ወዳጆና ከአርቲስት ዓለማየሁ ገብረህይወት ጋር


በአንዳንዶች የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ አባት የሚል የቁልምጫ ሥም የተሰጠው እውቁ ሙዚቃ ሰው ተሥፋዬ ለማ ባለፈው ሃሙስ ለሊት፥ ለአርብ አጥቢያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ተሥፋዬ ለማ «ኦርኬስትራ ኢትዮጵያ፤» በሚል ይታወቅ የነበረው የቀድሞውን የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ፥ የዛሬውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ሙዚቃ ባንድ በመራባቸው ዓመታት፥ የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ በአጠቃላይ የኅብረተሰቡንም ሆነ የሌሎች ተቀባይነትና ተሰሚነት ማስገኘት ባስቻሉ ሥራዎቹ ይወደሳል።

ተሥፋዬ ለማ ከኦርኬስትራ ኢትዮጵያ በኋላም በተለያዩ የሙዚቃ ተቋማት ባከናወናቸው ሥራዎቹ፥ ባፈራቸው ታዋቂ ድምጻውያን እና እንዲሁም ጥላሁን ገሰሰን ጨምሮ ለገናና ድምጻውያን በጻፋቸው የሙዚቃ ድርሰቶቹም ይታወቃል።

ተስፋዬ፥ የህክምና ክትትልና እገዛ ከሚያገኝበት የአዛውንቶች መኖሪያ ሳለ የደረሰውን በኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ ታሪክ ላይ ያተኮረ ዳጎስ ያሉ ገጾች ያሉት መጽሃፍ ለማሳተም ጥረት በማድረግ ላይ ሳለ ነው፥ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።

የአንጋፋውን የሙዚቃ ሠው ተሥፋዬ ለማን ህይወትና ሥራ ለመዘከር የተሰናዱትን ቅንብሮች ከዚህ ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ቆይታ ከሁለገቧ አርቲስት ዓለም ጸሃይ ወዳጆና ከአርቲስት ዓለማየሁ ገብረህይወት ጋር


Your browser doesn’t support HTML5

ቆይታ ከተሥፋዬ ለማ የእድሜ ልክ ወዳጅ፥ Charles Sutton ጋር