የራሱን ጫካ የፈጠረው - ድሬዳዋ

Your browser doesn’t support HTML5

አቶ በያን ተሰማ በድሬዳዋ ከተማ እስካሁን 260ሺ ችግኞችን የተከለ ሲሆን ወደፊት 3.5 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል በኬንያዊቷ ዋንጋሪ ማታይ የተያዘውን የ3 ሚሊዮን ችግኝ ሪከርድ ለመስበር ያልማል። ድሬዳዋ ከተማ ነምበርዋን በተባለ አካባቢ ቀድሞ የቆሻሻ መድፊያና ጎርፍ መውረጃ የነበረ ቦታን ወደጫካነት በመቀየሩ ሃገርቀፍ ተሸላሚ ሲሆን ለዓለምቀፍ ውድድርም አብቅቶታል።