በህወሓት መግለጫ ላይ የተሰጠ አስተያየት

  • እስክንድር ፍሬው

Your browser doesn’t support HTML5

"በህወሓት የወጣው መግለጫ ለውጡ ከመጣለት ሳይሆን ከመጣበት፣ ህዝብን የማይወክል አካል የወጣ ነው" ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅሕፈት ቤት የፕሬስ ኃላፊ ንጉሡ ጥላሁን በሰጡት ምላሽ ተናግረዋል። “ለዚህም ምክንያቱ መግለጫውን ያወጣው ቡድን በለውጡ ምክንያት የተቋረጠበት ጥቅም መኖሩና የነበረው ግፍ እንዲመለስ መመኘቱ ነው” ብለዋል።