ህወሓት ከሃገራዊው ገዥ ፓርቲ ራሱን አገለለ

Your browser doesn’t support HTML5

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ ከሃገራዊው ገዥ ፓርቲ እራሱን አግልሏል። ብልፅግና ፓርቲን በህገወጥነት የፈረጀው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ ለሁለት ቀናት የጠራውን አስቸኳይ ጉባዔ ትናንት ማምሻውን ሲያጠናቅቅ ባወጣው የአቋም መግለጫ ከፓርቲው ጋር እንደማይወሃድ አስታውቋል። ከኢህአዴግ ጋር የነበረውን ሃብትና ንብረት የማከፋፈል ሂደት በሕጋዊ መንገድ እንደሚፈፅም ገልጿል።