በአርሲ አካባቢ በስፋት ስለሚዘወተረው "ትሪ"

Your browser doesn’t support HTML5

በተለምዶ "ትሪ" በመባል የሚታወቀው የኦሮምኛ የባህል ዉዝዋዜ እና የዘፈን ስልት ቦኦሮምያ ክልል ምዕራብ እና ምስራቅ አርሲ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ አንዲሁም በባሌ አካባቢ በስፋት ይታወቃል። አራት ዓይነት የውዝዋዜ ስልት ያለው "ትሪ" በተለይ በሠርግ እና ታላላቅ ባህላዊ ክስተቶች ላይ ወጣቶች ይጫወቱታል። የምስራቅ አርሲ ዞን የባህል ጥናት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱልከሪም ቱቄ በዞኑ የተደራጁ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድኖች ለ"ትሪ" ማደግ አስተዋፅኦ እያበረከቱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የአሜርካ ድምፅ ባልደረባ ገልሞ ዳዊት ወደ ሻሸመኔ ከተማ ተጉዞ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።