ሬክስ ቲለርሰን አዲስ አበባ ናቸው

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን በአፍሪካ በሚያደርጉት የስድስት ቀናት ጉብኝት መጀመሪያ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። ሚስተር ቲለርሰን አፍሪካን ሲጎበኙ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ከተመረጡ ወዲህ የመጀመሪያው የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለሥልጣን መሆናቸው ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፕሬዚዳንት ትረምፕ በቅርቡ በአፍሪካ ሃገሮች ላይ የሠነዘሩትን ዘለፋ ያስተባብላሉ ተብሎ እየታሰበ ነው።