"በፌደራል ደረጃ ህጋዊ መንግሥት የለም" - ህወሓት

ፎቶ ፋይል፦ አቶ ጌታቸው ረዳ

በህዝብ ተወካዮች ምክርቤትና በፌደሬሽን ምክር ቤት እንደራሴ ሆነው የቆዩ አባላቱ ከዛሬ ጀምሮ እንደለሚለቁ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ አስታውቋል።

ፓርቲያቸው ከዛሬ ጀምሮ “በፌደራል ደረጃ ህጋዊ መንግሥት የለም” ብሎ እንደሚያምንና በሹመት በፌደራል መንግሥቱ ውስጥ የሚያገለግሉ ተሿሚ ባለሥልጣናት አባላቱም እንደሚለቅቁ የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል።

ክልሉ ከአሁን በኋላ በፌደራል ደረጃ የሚኖረው ግንኙነት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከሚሰጡና ከፍትህ ተቋማት ጋር ብቻ እንደሚሆንም አመልክተዋል።

በሌላ በኩል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕገመንግሥታዊ ሂደትን በጠበቀ ሁኔታ ምርጫውን ሰኔ 3/2013 ዓ.ም. ማራዘሙን ያስታወሱት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አደም ፋራህ “ለህገመንግሥቱ ተገዥ ያልሆኑና ሰላም የማይፈልጉ ቡድኖች ሕዝቡን የማወናበድ ሥራ እየሠሩ ይገኛሉ” ብለዋል።

አፈጉባዔው ይህንን መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ባደርጉት ቆይታ ነው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

Your browser doesn’t support HTML5

"በፌደራል ደረጃ ህጋዊ መንግሥት የለም" - ህወሓት