የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጉዳይ ጉባዔ በመቀሌ ተጀመረ

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ ክልል ለሚቋቋም ጊዜያዊ አስተዳደር ውይይት የሚደረግበት ጉባዔ ዛሬ በመቀሌ ተጀመረ።

ጊዜያዊ አስተዳደሩን ለማቋቋም የተመሰረተው ኮሚቴ ሰብሳቢ ሌተና ጄነራል ታደሰ ወረደ “ወደፊት ጊዜያዊ አስተዳደሩን የሚመሩ ባለሥልጣናት ከሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ተውጣጥተው የሥልጣን ክፍፍል ይደረጋል” ያሉ ሲሆን “የስልጣን ክፍፍሉ ሲጠናቀቅ ከፌዴራል መንግሥቱ ጋራ በጉዳዩ ላይ ድርድር ይካሄዳል” ብለዋል።

ጉባዔው “በአንድ ፓርቲ የበላይነት የሚካሄድ ነው” ያሉት በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ሦስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ እንደሌላቸው አስታውቀዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡