የንግድ ነዳጅ ወደ ትግራይ መግባት ጀመረ

Your browser doesn’t support HTML5

ከአንድ ዓመት ከስምንት ወራት በኋላ የንግድ ነዳጅ በቀጥታ ከጅቡቲ ወደ ትግራይ መግባት መጀመሩን የክልሉ የንግድና ላኪዎች ኤጀንሲ ገለፀ። የገባው ነዳጅ በክልሉ ካለው ፍላጎት አንፃር አነስተኛ በመሆኑ ማኅበራዊ አገልግሎትና ሕዝባዊ ትራንስፖርት ለሚሰጡ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው እንዲጠቀሙ መመሪያ ወቷል።