በትግራይ ክልል ሰፍኗል የተባለው ሕገ ወጥነት ወደ ሥርዓት አልባነት ሳያመራ በትብብር እንዲፈታ ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በትግራይ ክልል አለ ያሉት ችግር፣ በአንድ ፖለቲካ ፓርቲ ብቻ የሚፈታ አይደለም፤ ሲሉ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናንት ጀነራል ጻድቃን ገብረ ትንሣኤ ተናገሩ።

በጊዜያዊ አስተዳደሩ በተዋቀረ አጥኚ ግብረ ኀይል አስተባባሪነት፣ የክልሉን ፖለቲካዊ አስተዳደር የሚዳስስ ውይይት በመቐለ ከተማ ተካሒዷል።

በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ምሁራንና የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች በተሳተፉበት በዚኹ ውይይት፣ በክልሉ ያለው ችግር ምንጭ፣ ሕገ መንግሥቱን አክብሮ ያለመሥራት እንደኾነ፣ በመድረኩ በቀረበ ጥናት ላይ ተገልጿል፡፡