በትግራይ ክልል በመሰረተ ልማቶች ላይ ስለደረሰው ውድመትና ጉዳት ተገለጸ

Your browser doesn’t support HTML5

ትግራይ ክልል ውስጥ በተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ምክንያት በመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ በደረሰው ውድመትና በአገልግሎቶች መስተጓጎል ወደ 3ቢሊዮን ብር የሚገመት ጉዳት መከተሉን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ። ጉዳቱ ደረሰባቸው ከተባሉት ተቋማት ጋር በመቀናጀት ምርመራው ማካሄዱን የገለፀው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ያልተጠናቀቁ የምርመራ ሥራዎች እንዳሉ አመልክቷል።