ውጊያው በአክሱም ላይ የከበደ ጫና አሳርፏል

Your browser doesn’t support HTML5

በአለፉት ዓመታት መንፈሳዊ ተጓዦች እና ሀገር ጎብኝዎች በትግራይ ክልል ውስጥ ወደ ምትገኘው ቅዱስ ከተማ አክሱም ይተሙ ነበር። ዛሬ የዚህች ከተማ ብዙ ጎዳናዎች ጸጥታ ሰፍኖባቸዋል። በርካታ የንግድ ቤቶች ተዘግተዋል። የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ከሰባት ወራት በላይ የዘለቀው ብሄራዊው መንግሥቱና እና ገዢውን ፓርቲ ለሦስት አስርት ዓመታት ሲመራ የነበረው፣ ክልላዊው ፓርቲ የገቡበት ጦርነት ነው። በገጠሩ ክፍል ያለው ፍልሚያ በከተማዋ ላይ ያለውን ጫና እያከበደው ነው።