የኦሮሚያ ክልል የማኅበረሰብ ተወካዮች ለትግራይ የጦርነት ተጎጂዎች ድጋፍ አደረጉ

Your browser doesn’t support HTML5

የኦሮሚያ ክልል የማኅበረሰብ ተወካዮች፣ በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሚውል 10ሺሕ ኩንታል የምግብ እህል ርዳታ፣ ለክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስረከቡ፡፡

ከኦሮሚያ ክልል የማኅበረሰብ አካላት የተውጣጡ አባገዳዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሴቶች እና የወጣቶች ተወካዮች የተካተቱበት

ልኡክ፣ ከትላንት ሚያዝያ 17 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ቀናት፣ በመቐለ ከተማ ጉብኝት ያካሔዱ ሲኾን፣ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች እና ከመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ተወካዮች ጋራ ተወያይተዋል፡፡

የማኅበረሰብ ተወካዮቹን ስለ ጉብኝታቸው ያመሰገኑት፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ፣ በመንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት መካከል የተጀመረው

ንግግር ውጤታማ ይኾን ዘንድ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡ ተመሳሳይ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት፣ ከሌሎች ጎረቤት ክልሎች ጋራም ለማካሔድ እንደሚሠሩ፣ ፕሬዝዳንቱ አክለው አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡