በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ተጽዕኖ እያሳረፉ ነው

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ተጽዕኖ መፍጠራቸውን በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ ይገልጻሉ፡፡

በአዲስ አበባ ዙርያ በአካባቢ ጥበቃ ስራ የተሰማራው ሀብታሙ አዳነ በጸጥታ ችግሩ ምክንያት እንደልብ ተዘዋውሮ ለመስራት ባለመቻሉ ስራቸውን እስከማቆም የደረሱ ሰዎች ስለመኖራቸው ይናገራል፡፡

በአርባምንጭ ዩንቨርስቲ በተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ መምህር የሆኑት ዶክተር አዲሱ ፍቃዱ በበኩላቸው ግጭት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች አብረው እንደማይሄዱ ገልጸው በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶችም በብዝሃ ህይወት ሃብቷና ለቱሪስቶች በማስጎብኘት ገቢ የምታገኝባቸው በነበሩ ፓርኮችና የዱር እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡

በዚህ ዙርያ የተሰናዳውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ