ሕክምና ተምሮ ስራ አጥ መሆን ከባድ እና ቅስም ሰባሪ ነው የምትለው ዶ/ር ጽዮን ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ በፊት የቤት ለቤት ሕክምና ትሰራ እንደነበር ትናገራለች፡፡ ነገር ግን ህሙማኑን በመንከባከቡ ረገድ ቤተሰቦች ላይ ያለው ጫና፣ ለታማሚዎቹ የሚድረግ የእንክብካቤ ማነስ እና ኮቪድ 19 ይሄን እሷና ባልደረባዋን ዶ/ር ናትናኤል ሃይሉን ማዕከል እንድንከፍት አነሳስቶናል ትላለች፡፡
እቅዳቸው ተሳክቶም ከሶስት ወራት በፊት ከ 15 እስከ 20 ሰው የሚችል እና አምስት ነርሶች ያሉበት ግሬስ የሕሙማን እና የአረጋዊያን እንክብካቤ ማዕከልን ሊከፍቱ ችለዋል፡፡ በማዕከሉ የቤተሰብ አባል ያስገቡት ዶ/ር አታክልቲ በራኪ በማዕከሉ ያገኙት አገልግሎት እንዳስደሰታቸው ይበልጡን ደግሞ ማዕከሉ በባለሞያዎች መመራቱ እና ከሌሎች ሕክምና ማዕከሎች ጋር ኝኙነት ስላለው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ወ/ሮ ሃና ተስፋሚካኤል እናታቸው ታመው እቤት መዋል ከጀመሩ በኋላ ብቸኛ እንደሆኑባቸው ይናገራሉ፡፡ በተለይም ደግሞ እሳቸው ተማሪም ሰራተኛም መሆናቸው ለእናታቸው የሚያረካቸውን ያህል ድጋፍ ለማድረግ እንዳላስቻላቸው በመግለጽ ይሄን ማዕከል መኖሩ መስማቴ ሕይወቴን አቅሎታል ይላሉ፡፡
የማዕከሉ አጋር መስራች ዶ/ር ጽዮን ሰለሞን ዋናው ዓላማችን አዛውንቶች እና ሕሙማን በየግላቸው የሚያስፈልጋቸውን ነገር ተሟልቶላቸው፤ እንደ ሆስፒታል ሳይጨናነቁ ቤታቸው መስሏቸው እንዲቆዩ ነው ትላለች፡፡
Your browser doesn’t support HTML5