በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የህሙማን እና የአዛውንቶች ማዕከል የከፈቱት ወጣቶች አገልግሎታቸው

Your browser doesn’t support HTML5

ግሬስ የህሙማን እና የአዛውንቶች እንክብካቤ ማዕከልን እንድንከፍት ያደረገን ኮቪድ 19 ነው የምትለው ከመስራቾቹ መሃከል አንዷ ዶ/ር ጽዮን ሰለሞን ናት፡፡ ማዕከሉ አዛውንቶች እና ከሆስፒታል ውጭ እንክብካቤ የሚያሻቸው ታማሚዎች በነርሶች እየታገዙ እንዲታከሙ እንዲሁም ማህበራዊ ህይወታቸውን እንዲገፉ ያግዛል፡፡ በተለይም ስራ እና ትምህርት ኖሯቸው የሚወዷቸውን ማስታመም ያልቻሉ ሰዎች በማዕከሉ ስላገኙት ጥቅም አነጋግረናቸዋል፡፡