ወገኖቹን ያልዘነጋው የሐረር ልጆች ማህበር

Your browser doesn’t support HTML5

ድንበር የለሽ የሐረር ልጆች ማህበር በትውልድ ከተማቸው ሐረር ያሉ ወገኖቻቸውን ለመርዳት ባሰቡ የሰሜን አሜሪካ ነዋሪ የከተማዋ ተወላጆች የተመሰረተ ነው፡፡

ካለፉት ዓመታት ጀምሮ በሐረር ያለውን የንጹህ የመጠጥ ውሃ እጥረትን ጨምሮ በትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ያለባቸው የትምህርት ቁሳቁስ ችግር ከአባላቱ በሚያሰባስበው ገንዘብ እየደገፈ እንደሚገኝ የማህበሩ ፕሬደዳንት ዶክተር ማሾ አብርሃ ይናገራሉ፡፡

ባለፈው ዕሁድ እውቁ ተዋናይ አለማየሁ ታደሰን አምባሳደር አድርጎ የሰየመበት የማህበሩ አራተኛ የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ምሽት ቨርጂኒያ አሌክሳንድሪያ ውስጥ ተካሂዷል፡፡