በሱዳን ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ለሴቶች ጥበቃ እንዲደረግ ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በዓለም ዙሪያ ጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃትን ለማስቆም እየተካሄደ ያለውን ዘመቻ በማስመልከት ሱዳናውያን ሴቶች ካርቱም በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መስሪያ ቤት ውጪ ዕሁድ ኅዳር 18/2015 ዓ.ም ተቃውሞ አሰምተዋል።

ተቃዋሚዎቹ በሱዳን ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ለሴቶችና ህፃናት የተሻለ ጥበቃ እንዲደረግላቸውና ፍትህ እና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጠይቀዋል። በሱዳን በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች መከላከል ኃላፊ፣ በሀገሪቱ የሕግ አስከባሪዎች እጦት ምክንያት ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች መጨመራቸውን ገልፀዋል።