ሱዳናውያኑ ለመነጋገር ተስማሙ

Your browser doesn’t support HTML5

የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤትና ተቃዋሚዎቹ ተቋርጦ የነበረውን ውይይት ለማስቀጠል በሚያስችሉ አምስት ነጥቦች ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል። ወገኖቹ ለመነጋገር የተስማሙት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የጀመሩትን የማግባባት ሙከራ ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል። የስምምነቱን ጉዳይ ይፋ ያደረጉት በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደርና የሱዳን ዕርቅ ጉዳይ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር መሃመድ ድሪር ናቸው።