በሱዳን ጦርነት እየደረሰ ስላለው የባህላዊ ቅርሶች ውድመት ዐዲስ ሪፖርት ወጣ

Your browser doesn’t support HTML5

በጦርነት ላይ ባለችው ሱዳን፣ በአብያተ መዘክር እና በባህላዊ ሥፍራዎች ላይ እየደረሰ ስላለው ዝርፊያ እና ውድመት የሚዘረዝር ዐዲስ ሪፖርት ይፋ ሆኗል፡፡

ሪፖርቱን ያወጣው፣ ጦርነት በሚካሔድባቸው አካባቢዎች ያሉ ታሪካዊ እና ባህላዊ ቅርሶችን ከውድመት እና ከዘረፋ ለመጠበቅ የሚሠራው “ቅርሳ ቅርስ ለሰላም” (Heritage for Peace) የተባለው ገባሬ ሠናይ ድርጅት ነው፡፡ ከሱዳን ውጭ ያሉ ተቋማትም፣ ቅርሳ ቅርሱን፣ ጥበቃ ወደሚያገኙበት ቦታ በአፋጣኝ ማውጣት የሚያስችል ዕቅድ ለማዘጋጀት እየተጣደፉ ናቸው፡፡

ሄንሪ ዊልኪንስ ከቻድ ዋና ከተማ ከኢንጃሚና ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።