አፍሪካውያን ፍልሰተኞች በሱዳን ጠረፍ

Your browser doesn’t support HTML5

የሱዳን መንግሥት ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ወደሊቢያ አቋርጠው ሊገቡ የሞከሩ በርካታ ሱዳናውያን ጨምሮ አንድ መቶ ሰላሳ ስምንት አፍሪካውያን ፍልሰተኞችን ይዘናል ሲሉ አስታወቁ። ፈጥኖ ደራሽ እና ድጋፍ ኃይሎች ተብሎ የሚጠራው ሰራዊት አባላት፣ ሱዳንን ቻድን እና ሊቢያን በሚያዋስነው በረሃ ላይ ካሰሩዋቸው መካከል፣ ኢትዮጵያውያንና የቻድ ሰዎች እንዳሉባቸው ተናግረዋል።