የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት “ብሔራዊ ካዝናውን ሊጠቀልል ነው” መባሉን አስተባበለ

Your browser doesn’t support HTML5

የሱዳን ኢኮኖሚ በእጅጉ በመዳከም ላይ እንደኾነ የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ ማሻቀቡን የቀጠለው የዋጋ ግሽበት እንዲሁም፣ ምዕራባውያን አገሮች ለሱዳን ሰጥተው የነበረውን የዕዳ ቅነሳ ሥምምነት፣ ከመፈንቅለ መንግሥት በኋላ ማገዳቸው፣ ኢኮኖሚውን ክፉኛ አዳሽቆታል፡፡

ሄንሪ ዊልክንስ፣ ወታደራዊው መንግሥት፣ “ኢኮኖሚውን ጠቅልሎ ሊቆጣጠር እየሞከረ ነው፡፡ ዋግነር ግሩፕ ከተባለው የሩሲያ የግል ወታደራዊ ኩባንያ ጋራም ግንኙነት አለው፤” የሚሉትን ውንጀላዎች በሚመለከት፣ የሱዳን የገንዘብ ሚኒስትር ጂብሪል ኢብራሂምን አነጋግሮ የሚከተለውን ዘገባ አጠናቅሯል፡፡